Nigat Kokeb Primary and medium School
Announcement የ2019 ዓ.ም የተጓዳኝ ክበባትን (Co- Curricular Activities) ለማጠናከር የዕቅድ ውይይትና የሥራ አቅጣጫ ወይይት ተካሄደ

የ2019 ዓ.ም የተጓዳኝ ክበባትን (Co- Curricular Activities) ለማጠናከር የዕቅድ ውይይትና የሥራ አቅጣጫ ወይይት ተካሄደ

23rd September, 2026

የ2019 ዓ.ም የተጓዳኝ ክበባትን (Co- curricular Activities) ለማጠናከር የዕቅድ ውይይትና የሥራ አቅጣጫ ወይይት ተካሄደ


13/01/2019 ዓ.ም | ንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት

በዛሬው ዕለት 13/01/2019 ዓ.ም በንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የ2019 ዓ.ም የተጓዳኝ ክበባትን በተደራጀ፣ በተቀናጀና በውጤታማ መልኩ ለማስፈጸም ያለመ ሰፊ የውይይትና የሥራ አቅጣጫ መድረክ ተካሄደ።


መድረኩ በት/ቤቱ መሻሻል ም/ር/መ/ር አቶ ወንድይራድ አረጋ ስብሳቢነት የተካሄደ ሲሆን፣ የተለያዩ የክበባት አደረጃጀት ተጠሪዎች በመሳተፍ የ2019 ዓ.ም የክበባት እንቅስቃሴን በተመለከተ ሰፊ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።


የውይይቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች፦


በዕለቱ የተካሄደው ውይይት በሁለት ዋና አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ነበር።


1. የ2019 ዓ.ም ክበባትን ተግባርና ሐላፊነት ማስተዋወቅና ማሳወቅን በተመለከተ፡


በመጀመሪያው አጀንዳ የ2019 ዓ.ም በት/ቤቱ የሚንቀሳቀሱ ተጓዳኝ ክበባት በተማሪዎች ዘንድ በበቂ ሁኔታ እንዲታወቁና ተማሪዎች ከፍላጎታቸውና ከችሎታቸው ጋር የሚስማማውን ክበብ መርጠው በንቃት እንዲሳተፉ ስለሚደረጉ የማስተዋወቂያና የማሳወቂያ ሥራዎች ውይይት ተደርጓል።


ክበባት ከመደበኛው የክፍል ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎች እውቀታቸውን እንዲያሰፉ፣ ተግባራዊ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ የቡድን ሥራ ባህላቸውን እንዲያጎለብቱ እና የአመራር ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚያግዙ የተማሪ ተኮር መድረኮች መሆናቸው ተገልጿል።


2. የክበባት ዕቅድ ውይይትና የሥራ አቅጣጫ መስጠትን በተመለከተ፡


በሁለተኛው አጀንዳ የእያንዳንዱ ክበብ የ2019 ዓ.ም ዕቅድ በግልጽ ዓላማ፣ በተግባራዊ እንቅስቃሴ፣ በጊዜ ሰሌዳና በሚለካ ውጤት ላይ እንዲመሠረት የሥራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።


ክበባት የተማሪዎችን ፍላጎት፣ ችሎታና የዕድሜ ደረጃ በማገናዘብ ተግባራዊ የሆኑ ዕቅዶችን እንዲያዘጋጁ፣ በዕቅዳቸው መሠረት በተከታታይ እንዲሠሩ እና የሥራቸውን አፈጻጸም በየጊዜው እንዲገመግሙ ትኩረት ተሰጥቷል።


በ2019 ዓ.ም የሚንቀሳቀሱ የተጓዳኝ ክበባት


በት/ቤቱ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ክበባት የተማሪዎችን ሁለንተናዊ እድገት በሚያግዝ መልኩ የተደራጁ ሲሆን፣ እነሱም፦


1. የሥርዓተ ፆታ ክበብ

2. የተማሪዎች መማክርት ክበብ

3. የግብረ-ገብና ፀረ-ሙስና ክበብ

4. የገቢዎች ጉምሩክ ክበብ

5. የሰላም ክበብ

6. የንቃት ሕግ ክበብ

7. የሰብዓዊ መብት ክበብ

8. የእስካውት ክበብ

9. የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክበብ

10. የሒሳብ ክበብ

11. የሚኒ-ሚዲያ ክበብ

12. የባህልና ኪነ-ጥበብ ክበብ

13. የንባብ ክበብ

14. “ሐገርህን ዕወቅ” ክበብ

15. የመንገድ ደህንነት ክበብ

16. የጤና፣ ፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ፣ የበጎ አድራጎትና ቀይ መስቀል ክበብ

17. የስፖርት ክበብ

18. የሥነ-ምግብ ክበብ

19. የአካባቢ እንክብካቤ ተጓዳኝ ክበብ

20. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ክበብ

21. የእጅ ሥራ ክበብ

22. የግብርና፣ ዕርሻና ዕርባታ ክበብ


ተጓዳኝ ክበባት ለተማሪዎች ያላቸው ሚና


ተጓዳኝ ክበባት ተማሪዎች ከመደበኛ የክፍል ትምህርት ያገኙትን እውቀት በተግባር እንዲያውሉ የሚያስችሉ አስፈላጊ የትምህርት ድጋፍ መድረኮች ናቸው።


በክበባት ተሳትፎ ተማሪዎች የመሪነት፣ የቡድን ሥራ፣ የፈጠራ አስተሳሰብ፣ የችግር መፍታት፣ የግንኙነትና የራስ-መተማመን ክህሎቶቻቸውን ማዳበር ይችላሉ። በተጨማሪም ክበባት የተማሪዎችን ተሰጥኦ ለመለየትና ለማሳደግ፣ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለማዳበር እና በት/ቤት ማህበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎን ለማጠናከር ጉልህ ሚና አላቸው።


የት/ቤቱ የቀጣይ አቅጣጫ


በውይይቱ መድረክ ላይ የክበባት ሥራ በስም ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ውጤት እንዲገለጽ፣ እያንዳንዱ ክበብ ግልጽ ዕቅድ እንዲኖረው፣ ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ፣ የክበባት እንቅስቃሴ በየጊዜው እንዲከታተልና እንዲገመገም አቅጣጫ ተሰጥቷል።


በተለይም የክበባት ተግባራት ከመማር ማስተማር ሂደት ጋር እንዲቀናጁ፣ ተማሪዎች በፈቃደኝነትና በፍላጎታቸው እንዲሳተፉ እና ክበባት በተግባር የሚታዩ ውጤቶችን እንዲያመጡ ትኩረት ተሰጥቷል።


በትብብር ወደ ውጤታማ የክበብ እንቅስቃሴ


የ2019 ዓ.ም የክበባት እንቅስቃሴ በተጠሪዎች፣ በመምህራን፣ በተማሪዎችና በት/ቤቱ አመራር በጋራ ትብብር የሚመራ ይሆናል። ዓላማውም ተማሪዎች በእውቀት ብቻ ሳይሆን በክህሎት፣ በፈጠራ፣ በሥነ-ምግባር፣ በማህበራዊ ኃላፊነትና በተግባራዊ ብቃት የበቁ እንዲሆኑ ማስቻል ነው።

“እውቀትን በክህሎት፣ ክህሎትን በተግባር፣ ተማሪን በተሳትፎ እናበረታታለን!”


ንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት

13/01/2019 ዓ.ም


.

Copyright © All rights reserved.

Created with