“ተስፋን እንትከል” / “ABDII HADHAABNU"
በዛሬው ዕለት 9/11/2018 ዓ.ም የትምህርት ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የ90ቀን እቅድ የሆነውን “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ር/መምህራን፣ መምህራን፣ የክረምት ተማሪዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ደማቅ የችግኝ ተከላ መርሀግብር በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ተካሄደ።
በዚሁ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ ላይ የት/ቤቱ ባለድርሻ አካላት አስተባባሪነት ለተማሪዎቻቸው በአርአያነት ቀዳሚ በመሆን፣ ተማሪዎች ለነገዋ አረንጓዴ ኢትዮጵያ ያላቸውን ተስፋ በጉልበታቸው በመግለፅ፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፦ ሂደቱን በማስተባበርና አብሮነትን በማጠናከር በንቃት ተሳትፈዋል።
ይህ መርሃ-ግብር የአካባቢን ስነ-ምህዳር ለመጠበቅ ካለው ጠቀሜታ ባሻገር፣ በትምህርት ማህበረሰብ መካከል ያለውን አንድነት እና ተፈጥሮን የመንከባከብ ባህል ይበልጥ ያሳደገ ውብ ሆኖ አልፏል።
በዕለቱ በቦታው ተገኝታችሁ ደከመን፣ ሰለቸን፣ ጭቃ ነው ፣ዝናብ ነው ሳትሉ በዚህ ልክ ሰርታችሁ መርሀ ግብሩን ያሳካቸሁ የት/ቤቱ አስ/ር ሰራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎችን ከልብ እናመሰግናለን።
ማሳሰቢያ፦ የዛሬ ተከላ የነገ ህይወት ነውና፤ የተተከሉት ችግኞች እንዲፀድቁና ለውጤት እንዲበቁ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ይሁን!!!










.