የእውቀት ሽግግር (Knowledge Transfer) መርሃ ግብር ተካሄደ
የንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በትምህርት ቤቱ የሚሰሩ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የሙያ እውቀትና ክህሎት እንዲዳብር በማሰብ የእውቀት ሽግግር (Knowledge Transfer) መርሃ ግብር አካሂዷል።
መርሃ ግብሩ ሰኞ ጠዋት 1፡30 ሰዓት፣ 18/01/2019 ዓ.ም. በመምህራን ማረፊያ (Staff Room) የተካሄደ ሲሆን፣ የእውቀት ሽግግሩን ያካሄዱት (የእውቀት ሐብት ባለቤት) መምህር አብዪ ደሴ (Abyu Desse) ናቸው።
የዕለቱ የእውቀት ሽግግር ርዕስ፦ Basic Computer Skills
በዕለቱ የቀረበው የእውቀት ሽግግር ዋና ትኩረት Basic Computer Skills (መሠረታዊ የኮምፒዩተር ክህሎቶች) ላይ ያተኮረ ነበር። መሠረታዊ የኮምፒዩተር ክህሎት ማለት ኮምፒዩተርን በቀላሉና በትክክል ለሥራ እና ለመማር መጠቀም የሚያስችሉ መሠረታዊ ዕውቀቶችና ተግባራዊ ክህሎቶች ናቸው።
በዚህም የኮምፒዩተር መሠረታዊ አጠቃቀም፣ የኪቦርድና ማውዝ አጠቃቀም፣ ፋይልና ፎልደር መፍጠርና ማደራጀት፣ ሰነዶችን መፍጠርና ማስተካከል፣ መረጃ መፈለግና መጠቀም የመሳሰሉ ክህሎቶች በሥራ ቦታ ውጤታማነትን ለማሳደግ ወሳኝ ናቸው።
የእውቀት ሽግግሩ በተለይም በትምህርት ሥራ ውስጥ ቴክኖሎጂን በተገቢው መጠቀም፣ የሥራ ሰነዶችን በቀላሉ ማዘጋጀት፣ መረጃን ማስቀመጥና ማደራጀት እንዲሁም የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን የሚረዱ ክህሎቶችን ለማጋራት ዕድል ፈጥሯል።
በመርሃ ግብሩ ርዕሰ መምህራን፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ተሳትፈዋል። የእውቀት ሽግግሩም ተሳታፊዎች ያላቸውን የዲጂታል ክህሎት እንዲያሳድጉና በሥራቸው ውስጥ የኮምፒዩተርን አጠቃቀም የበለጠ እንዲያሻሽሉ አስተዋፅኦ አድርጓል።
የእውቀት ማካፈል የጋራ እድገት መሠረት ነው!
እውቀትን እንካፈል፤ ክህሎትን እናሳድግ፤ የተሻለ የሥራ አፈፃፀምን እንገንባ!





.