Nigat Kokeb Primary and medium School
Announcement ምግቤን ከጓሮዬ

ምግቤን ከጓሮዬ

27th July, 2026

🌱 ምግቤን ከጓሮዬ፡ የመምህር ደረጀ ከበደ አርአያነት ለሌሎች መነሳሳት ሆነ

ንጋት ኮከብ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃና መካከለኛ ትምህርት ቤት ለሠራተኞቹ ባከፋፈላቸው የጓሮ አትክልት ዘሮች መሠረት፣ መምህር ደረጀ ከበደ በቤታቸው ባለው ውስን የጓሮ ስፍራ ዘሮቹን በመዝራትና በትጋት በመንከባከብ አስደናቂ የልማት ውጤት አስመዝግበዋል።


ይህ ተግባር የመንግሥትን “ምግቤን ከጓሮዬ” እንቅስቃሴ በተግባር የሚያሳይ ሲሆን፣ በትንሽ ቦታም ቢሆን በቁርጠኝነትና በትጋት ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል በተግባር አረጋግጧል።


መምህር ደረጀ ከጓሯቸው ያገኙት ትኩስና ጤናማ የአትክልት ምርት ለቤተሰባቸው የምግብ ዋስትናን ከማጠናከሩም በላይ የቤተሰብ ወጪን በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምም አስገኝቷል።


የመምህር ደረጀ ተሞክሮ በትምህርት ቤቱ ሠራተኞችና በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተመሳሳይ የጓሮ ልማት እንዲስፋፋ የሚያበረታታ አርአያ ሆኗል።


🌿 የትምህርት ቤቱ ጥሪ


የጓሮ አትክልት ዘር የወሰዳችሁ የትምህርት ቤታችን ሠራተኞች በሙሉ፣ የመምህር ደረጀን አርአያ በመከተል ያከናወናችሁትን የጓሮ ልማት ውጤት በፎቶግራፍ በማስደገፍ እንድታጋሩን በአክብሮት እንጠይቃለን። የእናንተ ተሞክሮ ለሌሎች መነሳሳት ይሆናል፣ የ”ምግቤን ከጓሮዬ” እንቅስቃሴም የበለጠ እንዲጠናከር አስተዋፅኦ ያደርጋል።


“በትንሽ ቦታ ትልቅ ለውጥ!”

ንጋት ኮከብ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃና መካከለኛ ት/ ቤት

አዘጋጅ፦ የት/ቤቱ መሻሻል ም/ር/መ አቶ ወንድይራድ አረጋ እንደፃፉት

.

Copyright © All rights reserved.

Created with