12/01/2019 ዓ.ም | ንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት
በዛሬው ዕለት 12/01/2019 ዓ.ም በንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የመማር ማስተማር ሂደትን ይበልጥ ለማጠናከር፣ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎችና አጋር ክፍሎች የሚወጣቸውን ኃላፊነቶች በተቀናጀ መልኩ ለመፈጸም ከት/ቤቱ ተጠሪና ተወካይ መምህራን ጋር ሰፊ ውይይት ተካሄደ።
የውይይቱ መድረክ በት/ቤቱ መማር ማስተማር ም/ር/መ/ር አቶ ጉደታ ሆርዶፋ ሰብሳቢነት የተካሄደ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይ በተለይም የተጠሪና ተወካይ መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት፣ የስራ አፈጻጸም አቅጣጫ፣ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል እና የተማሪዎችን የመማር ውጤት ለማሳደግ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ተግባራት ዝርዝር ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጓል።
ውይይቱ በዋናነት፦
በውይይቱ ላይ የተለያዩ የት/ቤቱን የመማር ማስተማርና የድጋፍ ሥራዎች የሚወክሉ ተጠሪና ተወካዮች ተሳትፈዋል። እነሱም፦
በመድረኩ በተለይ የእያንዳንዱ ክፍል ተጠሪ የራሱን ኃላፊነት በግልጽ መልኩ በመረዳት ከሌሎች ክፍሎች ጋር በመቀናጀት መስራት ስለሚኖርበት ሁኔታ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም የተማሪዎችን የመማር ሁኔታ በተከታታይ መከታተል፣ የመምህራንን የትምህርት አፈጻጸም በትብብር ማሻሻል፣ የትምህርት ቁሳቁሶችንና የት/ቤቱን ሀብቶች በአግባቡ መጠቀም፣ የተማሪዎችን ፍላጎትና ተሳትፎ ማሳደግ እንዲሁም ችግሮችን በጋራ በመፍታት የትምህርት ጥራትን ማሻሻል ላይ ሰፊ ሃሳብ ተለዋውጧል።
ተሳታፊዎችም በየክፍላቸው የሚገኙ የስራ ሁኔታዎችን፣ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችንና ሊወሰዱ የሚገባቸውን የመፍትሔ አቅጣጫዎች በማንሳት ገንቢ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ከተነሱት ዋና ሃሳቦች መካከል የተማሪዎች ውጤታማ ትምህርት የአንድ ክፍል ወይም የአንድ መምህር ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የመላው የት/ቤት ማህበረሰብ የጋራ ኃላፊነት መሆኑ ተጠቅሷል።
ስለሆነም የት/ቤቱ ክፍሎች በቅንጅት፣ በትብብርና በጋራ ተጠያቂነት በመስራት የተማሪዎችን የመማር ውጤት ማሻሻል፣ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እና ተማሪዎችን በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የበቁ ዜጎች ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።
ንጋት ኮከብ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የመማር ማስተማር ጥራትን ማሻሻል፣ የመምህራንን ሙያዊ ተሳትፎ ማጠናከር እና ተማሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲማሩ ምቹ የትምህርት ሁኔታ መፍጠር ላይ የሚያደርገውን ጥረት ይቀጥላል።
“በትብብር እንሰራ፤ በጥራት እናስተምር፤ በውጤት እንደግ!”




.