Nigat Kokeb Primary and medium School
Announcement የክረምት የማስ ስፖርት መርሐ-ግብር

የክረምት የማስ ስፖርት መርሐ-ግብር

17th July, 2026

ንጋት ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የክረምት የማስ ስፖርት መርሃ ግብርን በተሳካ ሁኔታ አካሄደ።


በንጋት ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በዛሬው ዕለት 10/11/2018 ዓ.ም የትምህርት ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የ90ቀን እቅድ የሆነውን የማስ ስፖርት (Mass Sport) ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር ከት/ቤቱ መ/ማ/ም/ር/መ ከአቶ ጉደታ ሆርዶፋ፣ ከት/ቤት/መ/ም/ር/መ ከአቶ ወንድራድ አረጋ እና ከስፖርት ሳይንስ መምህሩ በመምህር መሳይ ሰሙ አስተባባሪነት በክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በሚማሩ ተማሪዎችን እና መምህራንን በማሳተፍ በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል።


የማስ ስፖርት ተማሪዎች ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን እንዲያዳብሩየአካል ብቃታቸውን እንዲያሻሽሉ እና ለዕለታዊ የትምህርት ተሳትፎ የሚያስፈልገውን ኃይልና ትኩረት እንዲጨምሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነበር። በመርሃ ግብሩ ወቅት ተማሪዎችና መምህራን በጋራ የተለያዩ የአካል ብቃት ልምምዶችን ሰርተዋል።


የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ለተማሪዎች በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፤ መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ የአካልና የአእምሮ ጤናን ያጠናክራልትኩረትንና የማስታወስ ችሎታን ያሻሽላልድካምንና ጭንቀትን ይቀንሳል፣ በትምህርት ክፍል ውስጥ የመማር ፍላጎትንና የትምህርት ውጤትን ከፍ ለማድረግም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል። 


ትምህርት ቤቱ ከትምህርት ጥራት ጎን ለጎን የተማሪዎችን አጠቃላይ እድገት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የስፖርትና የጤና ማበልፀጊያ መርሃ ግብሮችን በቀጣይነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋግጣል።

“ጤናማ አካል፣ ብሩህ አእምሮ፣ የተሻለ የትምህርት ውጤት!”

.

Copyright © All rights reserved.

Created with