በንጋት ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የክረምት የፅዳት ንቅናቄ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ
ንጋት ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በክረምት ወቅት የአካባቢ ንፅህናን ለማሻሻል ያለመ የፅዳት ንቅናቄ አካሂዷል። በዚህ ንቅናቄ የትምህርት ቤቱ አመራሮች፣ መምህራን፣ አስተዳደር ሠራተኞች፣ የክረምት ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎች እና ሌሎች የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አባላት በንቃት ተሳትፈዋል።
ቀደም ሲል በቆሻሻ የተከማቸ እና ለአካባቢው ውበትና ጤና ስጋት የነበረው ቦታ በተደረገው የጋራ ጥረት/ ንቅናቄ ሙሉ በሙሉ ተጽድቶ ንፁህና ማራኪ አካባቢ ሆኗል። ይህ ተግባር የአካባቢ ንፅህናን ከማሻሻል ባለፈ የትብብር፣ የተጠያቂነት እና የአካባቢ ጥበቃ ባህልን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
ትምህርት ቤታችን ወደፊትም ንፁህ፣ አረንጓዴና ለትምህርት ምቹ አካባቢ ለመፍጠር የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር በቅርበት በመስራት ተመሳሳይ ማህበራዊ ተግባራትን ይቀጥላል።
"ንፁህ አካባቢ ለጤናማ ትውልድ፣ የጋራ ኃላፊነት ነው!"









.