🌱 ተስፋን እንትከል!
3ኛ ዙር የ90 ቀን ዕቅድ የክረምት የበጎ ፍቃድ የአበባ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በንጋት ኮከብ ትምህርት ቤት ተካሄደ።
በንጋት ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ3ኛ ዙር የ90 ቀን ዕቅድ አካል የሆነው “ተስፋን እንትከል” የክረምት የበጎ ፍቃድ የአበባ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በትምህርት ቤቱ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች፣ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ እንዲሁም ከወረዳ 06 የመጡ ባለሙያዎችና ቡድን መሪዎች በመሳተፍ የአበባ ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴና ውብ የትምህርት ቤት አካባቢ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
የመርሀ ግብሩ ዋና ዓላማ የትምህርት ቤቱን አካባቢ በአበባና በአረንጓዴ ልማት ማስዋብ ብቻ ሳይሆን፣ በተማሪዎችና በመላው የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ዘንድ የአካባቢ ጥበቃ ባህል፣ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና የጋራ ኃላፊነት እንዲጎለብት ማድረግ ነው።
🌱 ዛሬ የተተከለው ችግኝ የነገ ውብ አካባቢ ተስፋ ነው!
በመሆኑም “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ የበጎ ፍቃድ ተግባር ተማሪዎች አካባቢያቸውን እንዲወዱ፣ እንዲጠብቁ እና ለዘላቂ አረንጓዴ ልማት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያበረታታ ትርጉም ያለው ተግባር ሆኖ ተከናውኗል።
“ተስፋን እንትከል፤ አረንጓዴ ነገን እናፍራ!” 🌿🌸











.